top of page
Search

አንጋፋው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ አረፈ

  • Dawit Eyayu
  • Oct 5, 2015
  • 1 min read

በሐገር ቤት ከማስታወቂያ ሚኒስትር ጀምሮ እስከ ጦቦያ መጽሄት አዘጋጅነት ሰርቶ በኋላም በስደት በኢሳት ላይ በመስራት ላይ ይገኝ የነበረው አንጋፋው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ ማረፉ ተሰማ::

ጸጋዬ ገብረመድህን አረአያ በሚል የብዕር ስም በጦቤያ መጽሔት ላይ ሲጽፍ ተወዳጅነትን ያገኘው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ በቨርጂኒያ ሕይወቱ ያለፈው ድንገት ነው ተብሏል:: አንጋፋው ጋዜጠኛ ትናንት ከጓደኞቹ ጋር አብሮ ያሳለፈ ሲሆን ቤቱ ገብቶ ከተኛ በኋላ በዛው ነው ሕይወቱ አልፎ የተገኘው::


 
 
 

Commentaires


Recent Posts
Follow Us
  • Facebook Basic Square
  • Twitter Basic Square
  • Google+ Basic Square
  • w-facebook
  • Twitter Clean
bottom of page