Search
ኢሳት በናይል ሳት ስርጭቱን ማድረስ ጀመረ ።
- Dawit Eyayu
- Oct 2, 2015
- 1 min read
ኢሳትን ከአየር ላይ ለማውረድ ባለፉት 5 አመታት ውስጥ ከ15 ግዜ በላይ የማፈን ሙከራ የተካሄደት ቢሆንም በጠንካራ አገር ወዳድ ኢትዮጲያውያን ትግል ለአየር መብቃቱን ዜና አስመክቶ የኢሳት አለማቀፍ ተጠባባቂ ዳይሬክተር የሆነው አርቲት ታማኝ በየነ በጉጉት ሲጠብቁ ለነበሩ የኢሳት ተመልካች እና አድማጮች ትናንት መስከም 20 2008 ዓም አብስሮዋል።
በአፋኝ ወያኔ ስርአት መዳፍ ስር ወድቆ መረጃ ማግኘት የተነፈገውን ህዝባችንን መረጃ ለማድረስ ቀን ከሌት የሚተጋው ኢሳት ከትናንት ጀምሮ በተለምዶ ናይል ሳት ተብሎ በሚጠራው ሳተላይት ስርጭቱን ማስተላለፍ ጀምሮዋል ፣ ስርጭቱንም ለመከታተል የሚቀጥለውን መረጃ ይጠቀሙ ።
Satellite : EutelSat – E8WA at 8 Degrees West
Frequency: 12604 Horizontal

Symbol Rate: 27500 FEC: 5/6
Comments