የኢህአዴግ የስዊዲን አምባሳደር ወይንሽት ታደሰ የእንቁላል ድብደባ በከፍተኛ ሁኔታ ደረሰባት።
- ethioasylumseekers
- Sep 21, 2014
- 1 min read
በስዊዲን የሚገኙ ኢትዮጵያኖች ከዚህ በኋላ እንደድሮው በውጪ እየወጡ መዝናናት የለም በማለት አምባሳደሯን እንቁላል በመወርወር ከፍተኛ የሆነ ውርደት እንድተከናነብ አድርገዋል። አብረዋት የነበሩ የወያኔ ጠባቂዎችም ራሳቸውን ከድብድባው ለማስመለጥ ሲሉ ጥለዋት ሄደዋል። የስዊድን ፖሊሶች በርካታ የፖሊስ መኪናዎችን በማምጣት ጸጥታውን ለመቆጣጠር የቻሉ ሲሆን ከረጅም እገታ በኋላ በፖሊሶች እርዳታ ከመኪናዋ ወጥታ ለመሄደ ችላለች።
እንቁላል አትጨርሱ ዛሬ የባንዳዎች እና የነነዋይ ውርደት በእንቁላል ቢጫ እናደርጋቸዋለን እና እሷ ላይ ብቻ አትጨርሱ፣ መኪናው የእንቁላል ጌጥ በዛበት የሚል አስቂኝ ክስተቶችም ነበሩበት። በውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያኖች በተጠናከረ መልኩ የወያኔን ባለስልጣናት በሄዱበት የማዋረድና እጃቸው ደም የተበከለ መሆኑን በተደጋጋሚ እየተነገራቸው ሲሆን በቅርቡ በተመሳሳይ ሬድዋን ሁሴን በዋሽንግተን ዲሲ የደረሰበት ውርደት ይታወሳል።
በአሁኑ ሰአት በርካታ የወያኔ ባለስልጣኖች ወደ ውጪ መጓዝን እንደማይመርጡ የደረሰን ሪፖርት ያመላክታል።
በስዊዲን የኢትዮጵያ አምባሳደር ላይ የገማ አሳና እንቁላል እንዳይወረወርባቸው ሲከላከሉ የሚያሳይ ፎቶ ነው
コメント