Search
በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ንብረቶቻቸው ተዘረፉ
- ethioasylumseekers
- Apr 8, 2014
- 1 min read
ኢሳት ዜና: - ኖርዝ ዌስት ውስጥ ቡልም ኦፍ በምትባል ከተማ ውስጥ የሚገኙ ከ 100 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ሱቆች ተዘርፈው ተቃጥለዋል. የከተማው ነዋሪዎች ከመሰረታዊ ልማት ጋር በተያያዘ ያስነሱትን ተቃውሞ ተከትሎ ረብሻ መፈጠሩንና ኢትዮጵያውያን, ሶማሊያውያንና ፓኪስታናውያን ኢላማ መሆናቸውን ተናግረዋል. ኢትዮጵያውያኑ አካባቢውን ለቀው ወደ ተለያዩ ቦታዎች ተሰደዋል. በከተማዋ የሚታየው ግጭት ተባብሶ መቀጠሉንም ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል.
Comments