top of page
Search

የኤርትራ መንግስት ከእኛ ጋር ለመታረቅ ከፈለገ ከጉያችን ያሉ የኤርትራ ተቃዋሚዎች ምን ይሆናሉ ብለን አንሰጋም ሲሉ አንድ የኢትዮጵያ መንግስት መንግስት ከፍተኛ

  • Writer: ethioasylumseekers
    ethioasylumseekers
  • Apr 2, 2014
  • 1 min read

ኢሳት ዜና :-በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የፐብሊክ ዲፕሎማሲና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ጄኔራል አቶ ጌታቸው አረዳ እንደተናገሩት ” የኤርትራ መንግስት ሃሳቡን ቀይሮ ወደ ሰላም ቢመጣ የኢትዮጵያ መንግስት ችግር የለበትም። የኤርትራ ተቃዋሚዎች ከጉያችን ስላሉ ምን እንሆናለን የሚል ስጋት የለብንም” በማለት ተናግረዋል። የታጠቁ የኤርትራ ሃይሎች እርምጃ የማይወስዱት በድንበር አካባቢ የኤርትራ ሰራዊት በብዛት ስላለ መሆኑን የገለጹት ጄኔራል ዳይሬክተሩ፣ የኤርትራ መንግስት ከእኛ ጋር ለመስማማት ከፈለገ ምንም ቂምና ቁርሾ የምንይዝበት ነገር አይኖርም ሲሉ አክለዋል። ኢትዮጵያ 20 ሺ ኤርትራውያን ስደተኞችን ታስተምራለች የተባለውም የተጋነነና ቁጥሩ ከ1800 እንደማይበልጥ የተናገሩት አቶ ጌታቸው፣ እነዚህ ተማሪዎች የጸጥታ ስጋት እንደማይሆኑና አስፈላጊው ምርመራ ተካሂዶባቸው ትምህርት እንደጀመሩ ገልጸዋል። ከኤርትራ ስደተኞች ይልቅ የጸጥታ ስጋት የሚፈጥረው የኢትዮጵያ ተስፋ የቆረጠው ወጣት ነው ያሉት አቶ ጌታቸው፣ ይህን ወጣት መከታተል የጸጥታ ችግሮችን እንደሚቀርፍ ገልጸዋል። በንግግራቸው መሃል ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ባይከብርም የመክፈር ፍላጎት እንዲኖረው በማድረጋችን ጸጥአየትኩረት አቅጣጫውን ለማስቀየር ችለናል ብለዋል። የጅቡቲ ወደብን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ደግሞ፣ ለጅቡቲ ወደብ የምንከፍለውን ኪራይ የጅቡቲ መሪዎች ቤተሰቦች የሚቀራመቱት በመሆኑ አገሪቱ ወደብ ትከለክለናለች ብለን አንሰጋም ሲሉ መልሰዋል።


 
 
 

Comments


Recent Posts
Follow Us
  • Facebook Basic Square
  • Twitter Basic Square
  • Google+ Basic Square
  • w-facebook
  • Twitter Clean
bottom of page