top of page
Search

ህዝቡ ለመለስ ፋውንዴሽን ገንዘብ እንዲያዋጣ እየተገደደ ነው

  • Writer: ethioasylumseekers
    ethioasylumseekers
  • Mar 14, 2014
  • 1 min read

መጋቢት 5ቀን 2006 ዓ/ም

ኢሳት ዜና :-የኢህአዴግ ካድሬዎች በተለይ በአዲስ አበባና በአጎራባች ከተሞች ባሉ ቤቶች እየዞሩ ለመለስ ፋውንዴሽን ማቋቋሚያ ከ50 ብር ጀምሮ እንዲከፍሉ እያስገደዱ ነው። እድሮች በነፍስ ወከፍ ከ8 ሺ ብር ጀምሮ እንዲከፍሉ መመሪያ ተላልፎላቸዋል። በዚህ መመሪያ የተሰላቹና የተበሳጩ ሰዎች “ወዴት እንሂድ” ሲሉ ለኢሳት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የመለስ ፋውንዴሽን በወ/ሮ አዜብ መስፍን ሊቀመንበርነት የሚመራ ሲሆን የአቶ መለስን አስከሬን በቋሚነት የሚያርፍበትን ቦታ የማዘጋጀትና ስራዎቻቸውን ለህዝብ የማቅረብ አላማ አለው። ምንም እንኳ መንግስት ለፋውንዴሽኑ ማሰሪያና ስራ ማስኬጃ በየአመቱ ገንዘብ የሚሰጥ ቢሆንም፣ ይህ ሳያንስ እያንዳንዱ ህዝብ ገንዘብ እንዲያወጣ መገደዱ አግባብ አለመሆኑን አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ። ገንዘብ መስጠትም ካለባቸው የኢህአዴግ ደጋፊዎች እንጅ ኢህአዴግን የማይደግፉት እንዲሰጡ መገደድ የለባቸውም ሲሉ እነዚህ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ። በእድሮች ላይ ሳይቀር የተጣለው የመዋጮ ግዴታ በበርካታ የእድር አባላት ላይ ቀርታ ፈጥሯል።


 
 
 

Comments


Recent Posts
Follow Us
  • Facebook Basic Square
  • Twitter Basic Square
  • Google+ Basic Square
  • w-facebook
  • Twitter Clean
bottom of page