top of page
Search

በአባይ ጉዳይ… ውጥረቱ ተባብሷል (የግብጽ እና ሱዳን ባለስልጣናት ሳይስማሙ ተለያዩ)(EMF)

  • Writer: ethioasylumseekers
    ethioasylumseekers
  • Mar 7, 2014
  • 1 min read

በያዝነው ሳምንት የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አሊ ከርቲ ከግብጹ አቻቸው ነቢል ፋህሚ ጋር በአባይ ጉዳይ ተነጋግረዋል:: በዚህ ስብሰባ ላይ የሱዳን እና የግብጽ ልኡካን ቡድን መግባባት ላይ አልደረሱም:: ይልቁንም ሱዳን ለኢትዮጵያ የምታግዝ መሆኑን በመግለጽ ግብጻውያን በሱዳኖቹ ባለስልጣናት ላይ ቅሬታቸውን ገልጸዋል::የሱዳኑ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አሊ ከርቲ ከግብጹ አቻቸው በተጨማሪ ከግብጹ ጊዜያዊ ፕሬዘዳንት አድሊ መንሱር ጋር ከመነጋገር ቀጠሮ ተይዞላቸው የነበረ ቢሆንም; ግብጻውያኑ ባለስልጣናት ገና ከመጀመሪያው ከሱዳኖቹ ጋር መስማማት ላይ መድረስ አልቻሉም:: አልፎ ተርፎም ግብጻውያኑ ሱዳኖቹ ላይ ወቀሳ አብዝተውባቸዋል:: “የቆየውን ወንድማማችነት ማቆየት አለብን” የሚል ማስጠንቀቂያ አዘል አባባል ነው ከግብጽ ባለስልጣናት ተደጋግሞ የሚሰማው::ሱዳን በኢትዮጵያ ግድብ ጉዳይ ጠንካራ አቋም ያልያዘች መሆኑን ግብጻውያኑ በተደጋጋሚ ይናገራሉ:: በዚህም ምክንያት… የሱዳኑ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አሊ ከርቲ ከግብጹ ፕሬዘዳንት ጋር ተይዞ የነበረውን ቀጠሮ ጭምር ሰርዘውታል:: ይህ ለሱዳኖች እንደስድብ የሚቆጠር ቢሆንም ወደ አገራቸው ከመመለስ ውጪ ሌላ አማራጭ አላገኙም::በሌላ በኩል ግብጽ በኢትዮጵያ ላይ ዲፕሎማሲያዊ ጫና ለመፍጠር የምታደርገውን ጥረት ቀጥላለች:: በሰራዊት ግንባታም በኩል በተለይ ከአሜሪካ በ’ርዳታ የሚሰጣት F 16 የጦር አውሮፕላኖች በበቂ ሁኔታ እየተዘጋጁ መሆናቸውን የግብጽ አየር ሃይል ምንጮችን በመጥቀስ የካይሮ ጋዜጦች እየዘገቡ ናቸው:: በተለይም ኢትዮጵያ ከአንድ ወር በኋላ ግድቡን ለመጀመር የሲሚንቶ አርማታ መሙላት የምትጀምረው በሚቀጥለው April ወር ላይ መሆኑ ግብጽ ውስጥ ውጥረትን ፈጥሯል::ባለፈው አመት የኢህአዴግ አስተዳደር ግንቦት 20 እስኪደርስ ጠብቆ የአባይ ወንዝን አቅጣጫ ቀይሮ እንዲሄድ በማድረግ የግድቡን ስራ መጀመሩ ይታወሳል:: ኢህአዴግ ግድቡን የኢትዮጵያ ህዝብ ከማድረግ ይልቅ የአንድ ፖለቲካ ድርጅት የስራ ውጤት በማድረግ የፖለቲካ ጥቅም እና ደጋፊ ለማግኘት የሚያደርገው ጥረት ብዙዎችን ቅር ሲያሰኝ የቆየ ነው::


 
 
 

Bình luận


Recent Posts
Follow Us
  • Facebook Basic Square
  • Twitter Basic Square
  • Google+ Basic Square
  • w-facebook
  • Twitter Clean
bottom of page