top of page
Search

ሳውድ አረቢያና ሌሎች የባህረ ሰላጤው ሃገራት ከግብጽ ጎን መቆማቸው ታወቀ

  • Writer: ethioasylumseekers
    ethioasylumseekers
  • Mar 7, 2014
  • 1 min read

የካቲት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞውን የግብጽ ፕሬዚዳንት ሙሃመድ ሙርሲን በመደገፍና በእርሳቸው ላይ የተወሰደውን እርምጃ በመቃወም ጠንካራ አቋም የያዘችውን ካታርን በዲፕሎማሲ ዘመቻ ለማግለል ሳውድ አረቢያና ሌሎች የባህረ-ሰላጤው አገራት ዲፕሎማቶቻቸውን ከአገሪቱ አስወጥተዋል። አዲሱ የግብጽ መንግስት የካታር ልኡካኑን ያስወጣ ሲሆን፣ ይህን ተከትሎም ሳውድ አረቢያ፣ ባህሬንና ዩናይት አረብ ኤምሬትስ ተመሳሳይ እርምጃ ወስደዋል።የግብጽ የፖለቲካ አካሄድ የአረብ አገራትን እየከፋፈለ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ግብጽ የአባይን ግድብ ግንባታ ለማስቆም የሳውድ አረቢያን ድጋፍ ጠይቃለች። ሳውድ አረቢያ እስካሁን ስለምትኢዘው አቋም ግልጽ አላደረገችም፣ ይሁን እንጅ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በግብጽና በሳውድ አረቢያ መካከል የተጀመረው መቀራረብ ሳውድ አረቢያ የግብጽን ጥያቄ በመቀበል በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ላይ እርምጃ ልትወስድ ትችላለች።


 
 
 

Comments


Recent Posts
Follow Us
  • Facebook Basic Square
  • Twitter Basic Square
  • Google+ Basic Square
  • w-facebook
  • Twitter Clean
bottom of page