የአውሮፕላን ጠለፋውና የህወሃት አመራሮች ስብሰባ
- ethioasylumseekers
- Feb 18, 2014
- 2 min read
የኢህአዴግ አመራሮች ለአስቸኳይ ጉዳይ ቤተመንግስት ተጠርተዋል:: ሊቀመንበሩን
የስብሰባውን አጀንዳ መናገር ጀመሩ:: ፎቶ ፋይል እንደምታውቁት መጪው 2007
የምርጫ ጊዜ ነው:: እና ጠላቶቻችን ከአሁኑ ምርጫው ; ፓርቲው እና አገሪትዋ ላይ
አደጋ ለማድረስ እየሞከሩ ነው:: ለዛ ምሳሌ የሚሆነው እና ዛሬ የተሰበብንበት
ምክንያት ትላንት የተጨናገፈው የአውሮፕላን ጠለፋ ነው:: ፓርቲያችን እንደ ትላንት
አይነቱ ጸረ-ልማት የሆነ ተመሳሳይ ተግባር እንዳይፈጸም ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ
አለበት:: ለዚህም አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ ይጠበቅብናል:: በእዚህ አጀንዳ
ላይ ያላችሁን አስተያየት ስጡና እንወያይበት:: አንዱ አመራር እጁን አወጣ::
እንዲናገርም ተፈቀደለት:: ሁሉም የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ጋር ፌዴራል
ፖሊስ መመደብ አለበት:: ለሚኒባስ ታክሲ አንድ ;ለአውቶቡስ ሁለት ከፊት እና
ከኋላ ይመደብ:: ምንም እንኳን ኢኮኖሚ ው የሚጎዳ ቢሆንም መጪው ምርጫ ላይ
ፈጽሞ አደጋ እንዲጋለጥ መፍቀድ የለብንም::>> እሱ ተናግሮ እንዳበቃ ሌላኛው እጁን አወጣ:: ይሄ የጠለፋ ተግባር ጥልቅ ምርመራ ያስፈልገዋል:: የጠለፋ ወንጀል ጉዳቱ የከፋ ነው:: ለዚህ አደገኛ የአሽባሪዎች ስራ ሊጋለጡ የሚችሉ የህብረተስብ አካላቶችን ለይተን ማውጣት አለብን:: ከዚህ ቀደም በሌላ የጠለፋ ወንጀል እንዲሁም ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎችን ፖሊስ የቅርብ ክትትል ሊያደርግባቸው ይገባል:: ሴት የጠለፉ ; ሊጠልፉ ሲሉ የተያዙ ; ወይም የሴት ጠለፋቸው የከሸፈባቸው ሰዎች ፖሊስ የትኩረቱ አካላት ያድርጋቸው:: ጠለፋ እንደሌሎች ወንጀሎች ተዛማጅ ነው:: ከዚህም አንጻር የሀገር ቀሚስ ጠለፋ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ለሴት ጠለፋ ወንጀል የተጋለጡ እንደሆነ ከዚህ በፊት የተደረገ ጥናት ያሳያል:: ስለዚህም ፖሊስ ጨርቆስ እና ሽሮሜዳ አካባቢ ያሉ ጥልፍ እና ቀሚስ ጠላፊዎችን ትኩረት ቢያደርግባቸው ክፋት ያለበት አይመስለኝም:: ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ እንዲሉ ለጠለፋ የሚያጋልጡ ቀዳዳዎች ን ሁሉ መድፈን አለብን:: ሌላኛው ቀጠለ ፓርላማው አሸባሪ ተብሎ ከፈረጃቸው ከእነ ግንቦት ሰባት እና አል-ሸባብ በተጨማሪ ጠላፊዎችን መጨመር ይጠበቅበታል:: ለዚህም ህግ አርቃቂው ኮሚቴ ህጉን እንዲያሻሽል ይደረግ:: ሌላኛው አከለ ለጥንቃቄ ያህል ከእንግዲህ አይሮፕላኖቻችንን ማብረር ያለባቸው የፓርቲ አባላቶች ብቻ መሆን አለባቸው::በተለይ ከፍተኛ ባለስልጣኖች የሚጓዙበት አይሮፕላኖች በታማኝ አባሎቻችን መሆን አለባቸው:: አባል ያልሆኑ ፓይለቶች ሆኑ ኮፓይለቶች እንዲሁም ሆስተሶች አባል የሚሆኑበት መንገድ ይመቻች:: አድር ባይ እና ኪራይ ሰብሳቢ ያልሆኑ ሀቀኛ የአይሮፕላን ሰራተኞች ማፍራት ይጠበቅብናል:: አባል መሆን የማይፈልጉ ወይም ተቃዋሚ ፓርቲን የመደገፍ ዝንባሌ የሚያሳዩ ሰራተኞች ከስራቸው መሰናበት አለባቸው:: በምትኩም ታማኝ እና አንጋፋ አባሎቻችን የማብረር ትምህርቱ ተሰጥቷቸው ስራውን እንዲቀላቀሉ ይደረግ:: ሌላኛው የህወሃት አመራር እንዲህ አለ ይሔ ጠለፋ የተካሄደው በጠላቶቻችን የተቀነባበረ ሴራ ነው:: ለካቲት 11ን የትግራይ ህዝብ እንዲሁም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በደስታ እንዳያከብር ለማድረግ ሆን ተብሎ የታሰበ ስለሆነ የህውሃት አባላት እና ደጋፊዎች እንዲሁም የብአዴን ; ኦህዴድ እና ድህአዴግ እንዲሁም አጋር ፓርቲዎች ጠለፋውን የሚያወግዝ ሰልፍ ህዝቡ እንዲወጣ የተለመደውን ቅስቀሳ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል:: አለ በስብሰባው መጨረሻ ፓርቲው ጠለፋውን የሚያወግዝ ጽሁፍ አውጥቶ እና ባለ ሰባት ነጥብ የአቋም መግለጫ ላይ በመወሰን አምራሩ ተበተነ:: በነጋታውም በከተማው የታክሲ እና አውቶቡስ ተሳፋሪ መጫኛ እና ማውረጃ ቦታዎች ላይ የፌዴራል ፖሊሶች ተመድበው ተሳፋሪው ጥብቅ ፍተሻ እየተደረገበት መሳፈር እና መውረድ ጀመረ::
Kommentarer